ቤቲ - ጂ በአገር ቤት አያሌ አድናቂዎች ያሏት፤ በአፍሪካ ደረጃም ሶስት የመላው አፍሪካ የሙዚቃ ሽልማቶች አሸናፊ ብትሆንም፤ የኦስሎ የኖቤል ሰላም ሽልማት ግና በዓለም አግኗታል።
የአገር ቤት አፍቃሪዎቿን ‘እሰይ’ አሰኝታበታለች። አዳዲስ አድናቂዎችም አፍርታበታለች።
ቀልቧ ለሙዚቃ የተገዛው ገና ለጋ ሕጻን ሳለች ነበር። የእናቷ ትኩረት ግና ትምህርቷ ላይ እንድትበረታ ነው። ምንም እንኳ በወቅቱ በልጅነት አዕምሮዋ በእናቷ አንደበት ተደጋግሞ የመነገሩ ጉዳይ ሚዛን ባይደፋላትም 12ኛ ክፍልን ጨርሳ በማስደሰት ወደ ሙዚቃው ዓለም ለመግባት ነበር ዕሳቤዋ። ግና፤ ከፍ ብላ ልብ ስትገዛና ወደ አዕምሮ ብስለት ስትሸጋገር ኮሌጅ በጥሳ ከአንድም ሁለት ዲግሪዎችን አግኝታለች።

Nobel Peace Prize ceremony 2019 - Oslo Source: Zimbio
ሰሞነኛ የሆነው የኦስሎው መድረክ ውስጧ ወሰን የሌለው ሐሴት ቢያሳድርም፤ ይልቁንም ስለ ሰላምዋጋ ልቀት፤ ስለምትቆምላቸው የስደተኞች ሕይወት አብዝታ እንድታስብ አድርጓታል።
በሙዚቃው ዓለምም ይህ ጅምሯ ከግራሚ ሽልማት የሚያደርሳት ጎዳና ሆኖ ታይቷታል።
ከመቼውም በበለጠ “ምኞትና ሕልሜ ግራሚ ማሸነፍ ነው” አሰኝቷታል።
ማን ተጠራጣሪ ይሆናል?

Grammy Source: Courtesy of NS
ቤቲ - ጂ በድምፃዊነቱ ብቻ የተወሰነች አይደለችምና ለመላው ኢትዮጵያውያን ወገኖቿ የምትመክረው፣ የምትለምነውና የምታሳስበው ብርቱ ጉዳይ አላት። ሲቃ የሚያሳድርባት፣ ነፍሷን ሰቅዞ የሚይዝባት ነገር።
የኢትዮጵያ ትልቅነትና የኢትዮጵያውንም ታላቅ ሕዝብነት።
ሆኖም፤ አሁን - አሁን “ትኩረታችንን ትናንሽ ነገሮች ላይ አድርገን መለያየታችንና መበታተናችንን ትተን እንደ አንድ ቤተሰብ ስንዋደድ የቀድሞ ግርማ ሞገሳችን ይመለሳል” ከሚል እሳቤ ላይ አድርሷታል።
እርግጥ ነው፤ የመጀመሪያ የተዋጣ የሙዚቃ ሥራዋ፤ ኋላም ድንቅ የተሰኘ አንድ የአልበም ዘፈኗ የተቃኘው እዚሁ አውስትራሊያ በሚገኘው ድምፃዊና ገጣሚ ናቲ ማን በመሆኑ አውስትራሊያ የመምጣት ፍላጎቷ ከፍ ያለ ነው።
ኢትዮጵያውያን - አውስትራሊያውያንም ቤቲ - ጂን መሻታቸው ዕውነት ነው።

Natty Man (L), and Betty G (R) Source: Courtesy of BG
ይትባሃሉ ‘ቸር ተመኝ፤ ቸር እንድታገኝ እንዲል።