በሕይወት ዘመናቸው "ኤርትራውያን ጀግናዎች ናቸው፤ ጥሩ ተዋጊዎች ናቸው። ለኢትዮጵያ ደማቸውን አፍስሰዋል፤ በኢትዮጵያ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ሰንደቅ ዓላማ ስር ወድቀዋል። "አንድነት ኢትዮጵያ" ብለው የሔዱ ናቸው" ያሉን የቀድሞው የሁለተኛው አብዮታዊ ሠራዊት አዛዥ፣ የብሔራዊ ውትድርና መምሪያ ኃላፊና የ "ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር" መጽሐፍ ደራሲ ብርጋዲየር ጄኔራል ውበቱ ፀጋዬ ሰሞኑን ከእዚህ ዓለም ተለይተዋል። ዝክረ መታሰቢያ ይሆናቸውም ዘንድ ቀደም ሲል በወርኃ ኖቬምበር 2014 ያካሔድነውን ቃለ ምልልስ ደግመን አቅርበናል።
አንኳሮች
- ከኮንጎ ዘመቻ እስከ ሰሜን ጦር ግንባር
- የጦር አካዳሚ በሀገር ውስጥና ሀገረ አሜሪካ
- የጀብዱ ሜዳል
- የቀይ ኮከብ ዘመቻ ክሽፈት አንኳር አስባቦች
Share






