"ከለበስኩት ልብስና መፅሐፍ ቅዱስ በስተቀር ምንም አልነበረኝም፤የተሰጠኝን አንሶላ ቀሚስ አድርጌ በእጄ ሰፍቼ ለብሻለሁ"ቤተልሔም ጥበቡ

Betelhem Tibebu Metro.jpg

Bethlehem Tibebu, Metro Train Ticket Inspector. Credit: B.Tibebu

ቤተልሔም ጥበቡ፤ ከጂግጂጋ ተነስታ፣ ከኢንዶኔዥያ በምታፈስ ትንሽዬ ጀልባ ውቅያኖስን አቋርጣ የአገረ አውስትራሊያን ምድር የረገጠችው አስከፊነቱ በብርቱ በሚነገርለት የናሩ ጥገኝነት ጠያቂዎች ማቆያ ለሁለት ዓመታት በዕግት ቆይታ ነው። የአውስትራሊያን ምድር ብትረግጥም ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት ከአግልሎ ማቆያ ማዕከል ማምለጥ አልቻለችም። *አስጨናቂ ታሪክ ሲሰሙ መንፈስዎ የሚታወክ ከሆነ ይህን ቃለ ምልልስ አያድምጡ፤ ከታች ያለውንም ፅሑፍ አያንቡ።


አንኳሮች
  • ከሰሎሞን ደሴቶች ወደ አውስትራሊያ
  • የመንፈስ ሁከት
  • የዳግም ሠፈራ ሕይወትና ትልሞች
ከናሩ ወደ ብሪስበን

ቤተልሔም ጥበቡ፤ ከሁለት ዓመታት የናሩ አግልሎ ማቆያ ማዕከል ምሬት የተመላበት ሕይወት በኋላ ለሕክምና ወደ ብሪስበን - አውስትራሊያ እንድትሔድ ተደረገ።

በ2015 ከናሩ ዕገታ ማዕከል በሕክምና አስባብ ብትወጣም ከብሪስበን አግልሎ ማቆያ ማዕከል ግና አላመለጠችም።

ብሪስበን እንደደረሰች ሕክምናዋን ጀመረች።

ለስድስት ወራት ያህል የመንፈስ ሁከቷ አልቀለልም።

ከመንፈቅ ሕክምና በኋላ ግና ትኩረቷ በሕይወት የመኖር ውሳኔ ላይ አረፈ።

በ2017 ለሁለት ዓመታት ተገልላ ከቆየችበት ማዕከል ነፃ ተለቀቀች።

ያለ ልዋጭ ገላዋን የሸፈነውን ልብስ ብቻ ለብሳ ናሩ የገባችውና ለመኝታ የተሰጣትን አንሶላ ሰፍታ ለመልበስ ግድ ተሰኝታለች የነበረችው ቤተልሔም፤ ብሪስበን ላይ አዲስ ሕይወት ጀመረች።

ራስን ችሎ የመኖር ጅማሮ ግና ግርታን ፈጠረባት።

ከአራት ዓመታት ራስን በራስ ማስተዳደር መለየት በኋላ የቴሌቪዥን፣የስልክ አጠቃቀምና ምግብ ማብሰል ጋር ራሷን ዳግም ማላመድ ያዘች።

ትንሽ ቆይታም ሌሎች ጥገኝነት ጠያቂና ስደተኞች እሷ ባለፈችባቸው የፈተና መንገዶች እንዳያልፉ የሰብዓዊ መብቶች ተቆርቋሪ በመሆን ድምጿን ማሰማት ጀመረች።

የብሪስበን ሕይወት እምብዛም ስላልጣማት ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ አያሌ ፍልሰተኞች ወደሚኖሩባት ሜልበርን ከተማ አመራች።

የዳግም ሠፈራ ሕይወቷ ከአውስትራሊያውያን ከመገለል፤ ከቶውንም አውስትራሊያውያን ተገቢ ቲኬት ይዘው በሕዝብ ትራንስፖርት ይጓዙ እንደሁ ተቆጣጣሪ ለመሆን በቃች።

መንገዱ ውስብስብና ረጅምም ቢሆን የፓርላማ አባል በመሆን ለአውስትራሊያውያን ማለፊያ የሕይወት ለውጥ ለማስገኘት ተልማ አለች።

የቤተልሔም ሕይወት ታሪክ መንፈስዎን ካወከ ወደ  Lifeline በ 13 11 14
 ወይም ወደ Beyond Blue 1300 22 4636 ይደውሉ።

Share
Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service