ሰላም በተለይም ባለፈው ወርሃ ሜይ 2022 የተካሔደው የአውስትራሊያ ፌዴራል ምርጫ ውስጧ ዘልቆ ገብቷል።
የፖሊሲ ቀረፃና ድንጋጌ አውጪነት ፖለቲካዊ ኃይል የሚሊዮኖችን ሕይወት ለትድግና ሊያበቃም ሆነ ለጉዳት ሊዳርግ እንደሚችል በቅርበት ተጠግታ በሌበር ፓርቲ የምርጫ ዘመቻ ቀስቃሽነት ተሳትፎዋ ወቅት ማየት ችላለች።

በግንዛቤ ጭበጣም አልተወሰነችም። ከቶውንም ራሷን ለአውስትራሊያ የሕግ መወሰኛ ወይም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልነት እስከ ማብቃት ትልም ደርሳለች።
ከራሷም አልፋ ሌሎች የማኅበረሰብ አባላትም ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ታበረታታለች።

'ችግር ሲደርስብን ብቻ ስንጮህ ም ማንም የሚሰማን የለም' ስትልም በዲሞክራሲያዊ ተሳትፎ ስለሚገኝ የተደማጭነትና ጉልህ ድምፅ ጠቀሜታን ታመላክታለች ።
ቁጭ ብለን ማማረር አንችልም። ተነስተን ተሳትፎ ማድረግ፣ ሌሎችንም መርዳት አለብን።ሰላም ፈለቀ ተገኝ
ለአርአያነትም በፌዴራል ምርጫ ዘመቻ ወቅት ስለ ድምፅ አሰጣጥ ዘዴዎች፣ የምርጫ ድምፅን ግላዊና ማኅበረሰባዊ ትሩፋቶችን እንዲያስገኙ ዕጩዎችንና ፖሊሲዎቻቸውን ለይቶ ስለማወቅ በማኅበራዊ ሚዲያ ገፆችዋ አስፍራ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ጥራለች ።
ሰላም በጋራ ለማደግ የአንድነትና ተሳትፎ ጠቀሜታን አፅንዖት ሰጥታ ታሳስባለች።
ሁላችንም በያለንበት ተለያይተን እንዴት ነው የምናድገው?
ከአንድነትና ትብብር ይልቅ የቅናት መንፈስን ማንገስ ወደፊት አራማጅ እንዳልሆነም ልብ ታሰኛለች።
'ሕዝባችን እንዲሳተፍ እፈልጋለሁ። መንግሥት እንድንሳተፍ ይፈልጋል። ያለ ተሳትፎ ለውጥ አይመጣም፣ ስትልም ታበረታታለች።






