"ከመማር ጋር ኃላፊነት አለ፤ የተማሩትን ለሌላው ማስተላለፍ የራስን ኃላፊነት መወጣት ነው። ለሕይወትም ትርጉም አለው።" ናዲያ ሞናያ

udnm.png

ISC building, Streatham Campus, University of Exeter, Exeter, Devon, England, UK / Nadia Monaia. Credit: Geography Photos/Universal Images Group via Getty Images / N.Monaia

ናዲያ ሞናያ - በሀገረ እንግሊዝ ኤክስተር ዩኒቨርሲቲ የሶስተኛ ዲግሪ (PhD) ተማሪ ናቸው። ውልደትና ዕድገታቸው አዲስ አበባ ነው። የኢትዮጵያዊት፣ ኤርትራዊትና ጣሊያናዊት ዝንቅ ብሔራዊ ማንነትን አጣምረው ይዘዋል። ሁለት ሀገርኛና አምስት የውጭ ሀገራት ቋንቋዎች ተናጋሪ ናቸው። የውልደት፣ ዕድገትና የትምህርት ሕይወታቸውን ነቅሰው ያጋራሉ።


ውልደትና ዕድገት

ወ/ት ናዲያ - ከአባታቸው ፔይትሮ ሞናያ እና ከእናታቸው ግላዲስ ይማም አብራክ የተከፈሉት አዲስ አበባ ከተማ ነው።

Nad kid pic.jpg
Nadia V. Pietro Monaia. Credit: NVP. Monaia

የበኩር ልጅ ናቸው። ተከታይ እህትና ወንድም አላቸው።

የዘመናዊ ሁለተኛ ደረጃ ቀለም ትምህርታቸውን እ.አ.አ በ1997 ያጠናቀቁት በሊሴ ገብረማርያም ትምህርት ቤት ነው።

Nad 2 High school.jpg
Nadia V. Pietro Monaia, High School Graduation from Lycee Guebre-Mariam Franco-Ethiopien. Credit: NVP.Monaia

በእዚያም አላበቁ፤ የከፍተኛ ተቋም ትምህርታቸውን ለመቀጠል ባሕር ማዶ ተሻገሩ።

የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ቀሰማ

ወ/ት ናዲያ ከሀገር ቤት ወደ ባሕር ማዶ ቀድመው ያቀኑት አንደኛው የማንነታቸው ጎን መፍለቂያ ወደ ሆነችው ሀገረ ጣልያን ነው።

የጣሊያኑ University of Trieste በሩን ከፍቶ ተቀበላቸው።

በመማሪያ ክፍሎቹም ዓለም አቀፍ እና የዲፕሎማሲ ሳይንስ አጠኑበት።

የሶስተኛ ዓመት ተማሪ ሳሉ የ Erasmus የፖለቲካ ሳይንስ ቋንቋዎች ፕሮግራም ነፃ ትምህርት ዕድል አሸናፊ ሆኑ።

ወደ ፈረንሳይ መዲና ፓሪስ አመሩ።

ዓረብኛ እና ማንዳሪን ቋንቋዎችን Institut National des Langues et Civilisations Orientales (INALCO) ዘልቀው በ2002 ከወኑ።

ለሶስተኛ ጊዜ ሀገር ቀየሩ። ሳዑዲ ዓረቢያ ገቡ።

በ2025 የእስልምናና ዓረብኛ ቋንቋ ጥናታቸውን መካ ከሚገኘው University of Umm Al-Qura በማዕረግ ተሸላሚ ሆነው ዲፕሎማቸውን ተቀበሉ።

ፊታቸውን ወደ አራተኛዋ ሀገረ አሜሪካ አዞሩ።

College of Southern Nevada ገቡ። በ2013 Associate of Arts (AA) in International Languages አጠናቅቀው የምሩቃን ተማሪዎች ተናጋሪ ጭምር ሆነው ተመረቁ።

ለጥቀውም ወደ አምስተኛዋ የትምህርት ቀሰማ መዳረሻቸው ሀገረ እንግሊዝ ውቅያኖስ አቋርጠው ደረሱ። የመጀመሪያ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በሥርዓተ ትምህርት ከ University of Derby እንዲሁም፤ ተጨማሪ የድኅረ ምረቃ ዲግሪያቸውን በፍልስፍና ከ University of Exeter በ2020 እና 2022 በቅደም ተከተል ተቀበሉ።

UD Nad.png
Nadia V. Pietro Monaia, graduation day with a Master of Arts in Education/TESOL Pathway from the University of Derby, UK. Credit: NVP. Monaia / University of Derby

በአሁኑ ወቅትም በሥርዓተ ትምህርት ላይ ያተኮረ የሶስተኛ ዲግሪ (PhD) ምርምር ጥናታቸውን ከሳዑዲ ዓረቢያ ሴቶችና መድብለ ባሕል ጋር አሰናስለው በማካሔድ ላይ ይገኛሉ።

የምረቃ ውጥናቸውን በ2027 አድርገው።

ከትምህርትና የአፍ መፍቻ ቋንቋዎቻቸው ጋር ተጣምረውም ሰባት ቋንቋዎችን ይናገራሉ።

ሀገር ቤት ሳሉ በእናት፣ በሴት አያትና አባታቸው አማካይነት አማርኛ፣ ትግሪኛና ጣሊያንኛ የአፍ መፍቻ ቋንቋዎቻቸው ነበሩ።

ፈረንሳይኛ፣ እንግሊዝኛና ማንዳሪን ቋንቋዎችን በትምህርት ቤት ሲካኑ፤ ዓረብኛን በትምህርት ቤትና በኑሮም ጭምር አርቅቀው ይናገራሉ።

ስንኝ ቋጣሪም ስለሆኑ፤ ግጥሞቻቸውን በእንግሊዝኛ፣ አማርኛና ዓረብኛ አራቅቀው ይፅፋሉ።

በሥራ ዓለምም ሳዑዲ ዓረቢያ ውስጥ በዩኒቨርሲቲ ደረጃ የእንግሊዝኛ ቋንቋ መምህርነት ሆነው ሠርተዋል።

በዲፕሎማሲው ዘርፍም በዓለም አቀፍ ግንኙነት መኮንነትና አስተባባሪነት በኦስሎ የሰላም ንግግር ላይ ተሳትፈዋል።

የትምህርትና የሥራ አገልግሎቶቻቸው በባሕር ማዶ ብቻ እንዲወሰኑ አይሹም።

ትምህርትን ማዕከሉ ያደረገውን የሶስተኛ ዲግሪ (PhD) የምርምር ጥናታቸውን ሲያጠናቅቁም ወደ ሀገረ ኢትዮጵያ ዘልቀው ትምህርት ተኮር ፕሮጄክቶችን ለመተግበር ዕሳቤውን ከወዲሁ ለንድፍ አብቅተዋል።

የትልቅ ግብር መነሻ ከብሩህ አዕምሮ የሚፈልቅ ትልም ነውና።

ሙያዬ በትምህርቱ ዘርፍ ስለሆነ 'እንደምን አድርገን ነው የትምህርት ተደራሽነት እንዲስፋፋ የምናደርገው? ሥርዓተ ትምህርቱንና የትምህርት ጥራትን የምናሻሽለው? በሚሉና ሴቶቻችንን በምንደግፍባቸው የተለያዩ ፕሮጄክቶች ውስጥ አስተዋፅዖ ማድረግን እሻለሁ።
ናዲያ ሞናያ - የሶስተኛ ዲግሪ (PhD) ተማሪ


Share

Recommended for you

Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now