በሥርዓተ ትምህርት፣ የሴቶችና መድብለ ባሕል ተኮር የሶስተኛ ዲግሪ (PhD) ምርምራቸውን በሀገረ እንግሊዝ ኤክስተር ዩኒቨርሲቲ እያካሔዱ ያሉት ወ/ት ናዲያ ሞናያ፤ ከፊል የምርምር ግኝቶቻቸውንና ፖሊሲ ነክ ጉዳዮችን አንስተው ያስረዳሉ።
አንኳሮች
- የሴቶች መብቶች
- ፍትሐዊነት፣ እኩልነትና አካታችነት
- ትኩረትን የሚሹ ምርምሮች
- የዩኒቨርሲቲ ንድፈ ሃሳብንና የገሃዱን ዓለም ዕውነታ የማዋደድ አስፈላጊነት
- ፆታዊ ትብብር
- ትምህርትና ሕብረተሰብ
በትምህርትና ሕብረተሰብ መሃል ክፍተት አለ። በቂ ግንዛቤ የለም። መፅሐፍ ላይ ይቀራል። ማኅበራዊ እርምጃ የለም። ያን ተመልክቻለሁ። ንድፈ ሃሳባዊ ምርምሮችን እንዴት ነው ወደ ተግባር የምንቀይረው? እኔ እንደማምነው፤ አንደኛው ቁሳችን ትምህርት ነው። በትምህርት ነገሮችን ማሻሻል፤ መቀየር እንችላለን።ናዲያ ሞናያ
የሴቶችን ጉዳዮች በተመለከተ ብዙ ጊዜ ምርምሮች የሚያተኩሩት ምዕራባውያን ሴቶች ላይ ነው። ምዕራባዊ አመለካከት ነው ያለው። የገጠር ሴቶች፣ የአፍሪካ፣ እስያ ወይም የሌሎች አኅጉራት ሴቶች ጉዳዮችን በተመለከተ ክፍተት አለ። የሴቶች ጉዳይ አውሮፓን ብቻ ማዕከል ያደረገ ጉዳይ አይደለም።ናዲያ ሞናያ
የሴቶች ጉዳይ በፍትሐዊነት፣ እኩልነትና አካታችነት ዕውን ሆኖ ባየው ደስ ይለኛል። ሆኖም፤ ዕውነታውንም ማየት እፈልጋለሁ። የሴቶች ጉዳይ ትልቅ ዓለም ነው። በአሁኑ ወቅት ያ አለ ለማለት እቸገራለሁ።ናዲያ ሞናያ
ታሪክን ወደ ኋላ መለስ ብለን የሴቶችን ጉዳዮች ስንመለከት ብዙ ለውጦች አሉ። ብዙ በሮች ተከፍተዋል። ሆኖም፤ ብዙ ሥራ ይጠብቀናል።ናዲያ ሞናያ
Share






