ዛሬ ማርች 23 ከቀትር በኋላ ጀምሮ የኮሮኖቫይረስ መዛመትን ለመገደብ የተጣሉትን አዳዲስ ገደቦች ሥራ ላይ መዋል ጀምረዋል። የተወሰኑ ግልጋሎቶቻቸው ግድ የማያሰኙ የንግድ ተቋማት ሲዘጉ፤ የገበያ አዳራሾችና ባንኮችን የመሳሰሉ ግልጋሎት ሰጪዎች ለሕዝብ ክፍት ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ። ቪክቶሪያ እገዳ የተጣለባቸው ግድ የማያሰኙ ግልጋሎቶችና እራሳቸውን እንዲያገሉ የተባሉ ግለሰቦች ውሳኔዎቹን በተግባር ማዋል - አለማዋላቸውን የሚቆጣጠሩ 500 ልዩ የፖሊስ ኃይል አሰማርታለች።
Share






