ዘመነ ኢሕአዴግ
የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢሕዲሪ) ሥርዓት በኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) በኃይል ተገርስሶ መውደቅን ተከትሎ፤ የጦርና የፖሊስ ሠራዊት አባላቱም ከመደበኛ ተግባራቸው ተገለሉ።
የሕግና ሥርዓት አስከባሪ ኃይሎች ክፍተት ተፈጠረ። ይህንኑ ክፍተት ለመሙላት አገዛዙ ከሕዝብ የተውጣጡ "የሰላምና መረጋጋት" ፀጥታ አስከባሪዎችን በየቀበሌና ከፍተኛዎች አቋቋመ።
አቶ ንብረት ዓለሙ የመኖሪያ ቀበሌያቸው የሰላምና መረጋጋት ሰብሳቢ ሆኑ።
ከበጎ ፈቃደኛ ተግባራቸው ጋር ተያይዞም በዘረፋ የተሰማሩ ሰዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ቻሉ። ግብራቸው በአገዛዙ ዘንድ ሞገስ አላበሳቸው።
አፍታም ሳይቆይ የጋዜጠኛነት ስልጠና ዕድል አገኙ። ስልጠናውን ወስደው ሲጨርሱ በሚዲያ ቃኚነት ተመደቡ።
ምደባው ከግል አተያያቸው ጋር አልሔድ አለ። ቅሬታቸውን ገልጠው የሥራ መደባቸውን በፈቃዳቸው ቢለቁ መዘዝ እንደሚያስከትልባቸው በመስጋት አገር ጥለው ኮበለሉ።
ጂቡቲ
የውድ አገራቸውን ኢትዮጵያ ድንበር አቋርጠው ጂቡቲ ገቡ። ጥገኝነት ጠየቁ። ጂቡቲ ለ15 ወራት የጥገኝነት ጠያቂና ስደተኛነት መጠለያቸው ሆነች።
በቆይታቸውም ወቅት በኮተቤ ኮሌጅ የእንግሊዚኛ ቋንቋ ዲፕሎማ ምሩቅነት ክህሎታቸው ለስደት አስተማሪነት አበቃቸው።
በለስ ቀንቷቸው ሲድኒ - አውስትራሊያ ሲዘልቁ፤ እኒያን የአገር ቤትና የስደት ጥምር የሥራ ልምዶች አውስትራሊያ ውስጥም በቀላሉ ሊጠቀሙባቸው እንደሚችሉ በማሰብ ከከፍተኛ በራስ መተመን ጋር ነበር።
አውስትራሊያ
ይሁንና የአውስትራሊያ ሠፈራ ኑሮ ጅማሯቸው ግና ከዕሳቤያቸው ጋር መሳ - ለመሳ አልሔደም።
ለየቅል ሆነ።
አያሌ የሥራ ማመልከቻዎችን ቢያስገቡም አሠሪዎች ከሥራ ገበታቸው የሚያቋድሷቸው አልሆኑም።
"ዘለግ አድርጎ የሚያንኳኳ፤ በር ይከፈትለታል" እንዲባል፤ አይታክቴነታቸው የ ሲድኒ ሞርኒንግ ሔራል ጋዜጣ ሕትመት ክፍል የደመወዝ መክፈያ ባሕር መዝገቡ ላይ ሊያሰፍፈራቸው ወሰነ።
ሠራተኛ ሆኑ።
ከስድስት ዓመታት በኋላ የሥራ ዝውውር ገጠማቸው። ወደ ባሌ ሳይሆን ወደ ሜልበርን ተዛወሩ።
ከውድ ባለቤታቸውና አራት ልጆቻቸው ጋር የአዲሱ ሥራቸው ዘ ኤጅ ጋዜጣ የሚታተምባት ሜልበር ከተማ ገቡ።

Nibret Alemu with his 48 years of wife, Fitfite Asrat. Credit: NA.Kassa
ለአቶ ንብረት፤ የሜልበርን በረከት በሥራና በልጅ ብቻ አልተወሰነም። በቪክቶሪያ ክፍለ አገር መንግሥት ነፃ የትምህርት ዕድል በአስተርጓሚና ተርጓሚነት የዲፕሎማ ባለቤት ሆነዋል።

Daniel Andrews, Premier of Victoria (L), and Nibret Alemu Kassa (R). Credit: NB.Kassa
አስከትለውም፤ በዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ልማት ዘርፍ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።

Nibret Alemu graduated from Victoria University with Bachelor's Degree in International Community Development. Credit: NB.Kassa
ተጨማሪ ያድምጡ

ንብረት ዓለሙ፤ ከሞጣ እስከ አውስትራሊያ