Watch FIFA World Cup 2026™

LIVE, FREE and EXCLUSIVE

"ዘውድ ቢኖር ኖሮ ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ደረጃ ላይ አትደርስም ነበር" አቶ ንብረት ዓለሙ

HSI.png
Emperor Haile Selassie I of Ethiopia (1892 - 1975), 1965. Credit: John Bulmer/Popperfoto via Getty Images

አቶ ንብረት ዓለሙ፤ የዘመነ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢሕዲሪ) በሥራ ዓለም ሕይወታቸው ያስከተለባቸውን ፖለቲካዊ መዘዝ አንስተው ይናገራሉ።


Published

Updated

By Kassahun Seboqa Negewo

Source: SBS



Share this with family and friends


አቶ ንብረት ዓለሙ፤ የዘመነ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢሕዲሪ) በሥራ ዓለም ሕይወታቸው ያስከተለባቸውን ፖለቲካዊ መዘዝ አንስተው ይናገራሉ።


ዘውድና ሪፐብሊክ

አቶ ንብረት የዘውድ ሥርዓቱን የተካው የጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ፤ ዘግይቶም ወደ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢሕዲሪ) የዞረው ሥርዓት ወዳጅና የማርክሲስት ሌኒንስት ርዕዮተ ዓለም አራማጅም አልነበሩም።

ከቶውንም የዘውዱ ሥርዓት በሪፐብሊክ የመተካት ጦስ ኢትዮጵያ ዛሬ ላለችበት የጎሣ ፖለቲካ ቀውስ መዳረግ አስባብ እንደሁ ያመላክታሉ።

በዘመነ ኃይለ ሥላሴ የነበረው ዲሞክራሲ ከዛሬው የአውስትራሊያ ዲሞክራሲ ይበልጥ እንደነበርም አመኔታቸውን ይገልጣሉ።

የዘመነ ደርግ መሬት ለአራሹ አዋጅም ለኢትዮጵያ ዋነኛ ቀውስ አንዱ ምክንያት ስለመሆኑና የባላባት ሥርዓት ኢትዮጵያን ያቆየ ነው በሚል አተያያቸውን ያጋራሉ።

በወቅቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች፤ ከተቃዋሚዎስ እስከ ገዢው ሰደድ ፓርቲና በኋልም የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ (ኢሠፓ) ያሉ ድርጅቶች በአባልነት እንዲቀላቀሉ ቢጠይቋቸውም ምላሻቸው እምቢታ ነበር።

ያም አስባብ ሆኖ በፀረ ማርክሲስት ሌኒንስት ተፈርጀው ከሥራ የኃላፊነት ደረጃቸው ዝቅ እንዲሉ ተደርጎ ከአዲስ አበባ ወደ ባሌ ለመላክ እንደበቁ ያወሳሉ።


Latest podcast episodes

Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now