በፐርዝ - ምዕራብ አውስትራሊያ ነዋሪ የነበሩትና ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የአቶ ታደለ ፈለቀ ቀብር ሥነ ሥር ዓት ዓርብ ዲሴምበር 29 / ታህሣሥ 19 ይፈፀማል። በፐርዝ ደብረ መድኃኒት መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ መንክራት ቆሞስ አባ ገሪማ "ታደለ ማለት ሀገር የሌለው፣ ብሔር የሌለው፤ የስደተኞች ተቀባይ፣ ለቤተክርስቲያን ሕይወቱን ያበረከተ ቅን አገልጋይ ነው። የኢትዮጵያ ምልክት ነው። 'መጋቢ ፍቅር ታደለ' ብለን የምንጠራው በሁሉም ዘንድ ተወዳጅ፣ አዛኝና ሩህሩህ በመሆኑ ነው" ሲሉ ገልጠዋቸዋል።
Share





