በትግራይ ግጭት ሳቢያ የተፈጠሩ የማኅበረሰብ ልዩነቶችን ለመፍታት ምን መደረግ አለበት?
“ኅብረተሰባችን መካከል መከፋፈል የጀመረው የጎሣ ፖለቲካ ከመጣ ጀምሮ ነው። ማንኛችንም የሚያራርቀንን ከማስፋት ይልቅ ሊያቀራርበን የሚችለውን ነገር እያሰብን፤ እንደ አንድ አገር ልጆች እየተመካከርን ችግሮችን መፍታት ነው።” አዳሙ ተፈራ
“የትግራይ ህዝብም ሆነ የትግራይ ተወላጅ የማንም ጠላት አይደለም። የሱን መብት ለማስከበር ይታገላል። የሌሎችንም መብት መንጠቅ አይፈልግም። የምንጠላው ሕዝብም የለም። ለሁሉም የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ክብር አለን።” ዶ/ር ፍሳሃ ኃይለ ተስፋይ
“ኢትዮጵያውያኖች የተገመድንበትን ድርና ማግ ፈትቶ የጣለው የጎሣ ፖለቲካ ነው። ወደ ኅሊናችን እንመለስ። ሰዎች ከሰብዕና ልዕልና ዝቅ ማለት የለባቸውም። የነቁ ወይም ዓይናቸውን የከፈቱ ሰዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ፊደል የቆጠሩ ዜጎችም ዕድሜ የጠገቡ አዛውንቶችም በዚህ ጉዳይ ላይ ጥሩ የሆነ ሚና ሊጫወቱ ይገባል።” አያሌው ሁንዴሳ

Adamu Tefera. Source: A.Tefera

Fisaha Haile Tesfay. Source: FH.Tesfay

Ayalew Hundessa. Source: A.Hundessa