አንኳሮች
- ተግዳሮቶች
- መንስኤዎች
- መዘዞች
የማኅበረሰብ አባላት ንቁ ተሳትፎ መጥፋት፣ የጎሳ ፖለቲካ፣ የቤተ ክርስቲያን ክፍፍል፣ የአመራር አባላት ክህሎትና ዲሲፕሊን ማነስ፣ ለቃሉ የሚያድርና ኃላፊነትን በብቃት ለመወጣት ዝግጁ የሆነ ሰው ጥቂት መሆን፤ ማኅበሩን ከጎዱ ችግሮች ውስጥ የሚጠቀሱ ናቸው።ደራሲ አዳሙ ተፈራ፤ የቀድሞው በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት፣
ማኅበሩን እንደራስ ጉልት ወይም ንብረት አድርጎ ማየት፣ የተለያዩ ቡድኖችን አሰባስቦ በማሳመፅ የተመረጡ ሰዎችን ማጥቃት፣ ብቃት የሌላቸውን ሰዎች መምረጥ፣ የብሔር ድርጅቶች መብዛት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ማኅበሩን ለመቆጣጠር የሚያደርጉት ሩጫ ከፍተኛ ተግዳሮቶች ሆነው ለማኅበሩ መዳከም ምክንያት ሆነዋል።አቶ ዓለማየሁ በዛብህ፤ የቀድሞው በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ዋና ፀሐፊ
ዋነኛ ችግሮቻችን፤ የማኅበሩን መተዳደሪያ ደንብ በተግባር አለማዋል፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የሰብዓዊ መብቶች ሲጣሱ ወደ ጎን ብሎ ማለፍና ለስፖርት ዋጋ አለመስጠት ናቸው።አቶ አሕመድ ዳውድ፤ የቀድሞው በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር የቦርድ አባልና ሥራ አስፈፃሚ (ዕገዳ ላይ)
አንዱ ችግር የአመራር አባል በመሆን አንድ ነገር አገኝበታለሁ ብሎ መግባትና ያ ሳይገኝ ሲቀር መጥፋት ነው።ዶ/ር ቢቾክ ዋን፤ በቪክቶሪያ ዩኒቨርሲቲ የማኅበራዊ ሳይንስ መምህር
ተግዳሮቶቹ፤ የመተዳደሪያ ደንቡን አለመፈፀም፣ አምባገነንነትና ግለኝነት መንገሥ፣ የማኅበረሰብ ተሳትፎ አለመኖር፣ በዘር ፖለቲካ ምክንያት ማኅበሩን የኢትዮጵያውያን ብሎ አቅፎና ደግፎ አለመያዝ፣ የቀድሞ አመራሮችን ተሞክሮዎች አለመጠቀምና ማኅበሩ የኢትዮጵያውያን ተቋም እንጂ የግል አለመሆኑን አለመለየት ናቸው።ደራሲ ታክሎ ተሾመ፤ የቀድሞው በታዝማኒያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት