“ ወንዶች ከሴቶች በሶስት እጥፍ ራሳቸውን ለማጥፋት የተጋለጡ ናቸው ”

Dr Gelaye Tadesse Source: GT
ዶ / ር ገላዬ ታደሰ በምእራብ አውስትራሊያ የካንትሪ ሄልዝ አገልግሎት የአእምሮ ጤና መምህር እና ሀኪም እንደሚሉት ከሆነ ወንዶች ከሴቶች በሶስት እጥፍ ራሳቸውን ለማጥፋት የተጋለጡ ናቸው ፡፡ ለዚህም ዋነኛው መንስኤ የአእምሮ ጤና መታወክ ሲሆን አብዛኛዎቹ ወንዶች ወደ እርዳታ ከመሄድ ይልቅ በውስጥ አምቆ መያዝን ይመርጣሉ ፡፡ በአንጻሩ ሴቶች እርዳታን የመጠየቅ እና መነጋገርን ስለሚመርጡ ለህመሙ በቶሎ መፍትሄን ያገኛሉ፡፡ እንደ አለም አቀፉ የጤና ድርጅት መረጃ ከሆነ በየአመቱ 80 ሺህ ሰዎች ህይወታቸውን ያጠፋሉ፡፡
Share