አገር ቤትና ባሕር ማዶ - “ሕልሜ ጠንካራ የኢትዮጵያዊነት መንፈስ እንዲያብብ ነው።” - አበበ ጽጌ

My Story Abebe Tsige

አበበ ጽጌ Source: Courtesy of AT

የሕይወት ጉዞ ከውልደት እስከ ዕድገት የራሷን ምዕራፍ እየከፈተችና እየዘጋች ትረማመዳለች። የትናንት ሕይወት - የዛሬ ትውስታ ይሆናል። ስለ መጪው የሚያውቅ የለም። ምኞትና ተስፋን ከማሳደር በስተቀር። የዛሬው “አገር ቤትና ባሕር ማዶ” ወር ተረኛ አቶ አበበ ጽጌ ናቸው። የሕይወት ጉዞ ትረካ መነሻቸው የትውልድ ቀዬአቸው ወልቂጤ ነው። በስደት ሕይወት ምልሰታዊ ምልከታቸው ወደ ሱዳን አሻግረው፣ በኒውዚላንድ አቋርጠው፤ የአገረ አውስትራሊያ ሕይወታቸውን ከኢሕአፓ ትግላቸው ጋር አጣቅሰው ያወጉናል።


አቶ አበበ በለጋ ሕይወታቸው የ1966ቱን የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮት ንቅናቄ ተከትሎ በወቅቱ ስመ ገነን የነበረው የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ወጣቶች ክንፍ የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ወጣቶች ሊግ (ኢሕአወሊ) አባል ሆኑ።

My Story Abebe Tsige
የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) Source: Courtesy of PD

እንደ ዘመናቸው ወጣቶች ኢትዮጵያን በሶሻሊስታዊ ሥርዓት ለመታደግ።

 ሆኖም፤ የመጨረሻው የኢትዮጵያ ዘውዳዊ የአገዛዝ ሥርዓት ሲያከትም ሥልጣነ መንግሥቱ በወቅቱ አዲስ በተመሠረቱት የፖለቲካ ድርጅቶች እጅ ሳይሆን በአገሪቱ የጦር ኃይሎች መዳፍ ስር ወደቀ።

 የወጣቱ አበበ ጽጌ ፓርቲ - ኢሕአፓም ዋነኛ የፖለቲካ ስልጣን ተቀናቃኝ ሆኖ ቀረበ። “ያለ ምንም ደም - ኢትዮጵያ ትቅደም” የተዘመረለት አብዮት አያሌ ወጣቶችን ለእሥራት፣ ስደትና ሕልፈተ ሕይወት ዳረገ።

 የወጣቱ አበበ ዕጣ ፈንታም እሥራትና ስደት ሆነ።

 የሱዳን አጎራባቿ ጎንደር፤ ለአቶ አበበ የኢትዮጵያን ድንበር በእግር መሻገሪያ ሆነች። የሱዳን ምድርም ወጣቱ አበበን ከባላገርነት ወደ ስደተኛነት ለወጠች።

 ለስደት ያበቃቸው ፖለቲካዊ አተያይና የኢሕአፓ አባልነታቸው ሱዳንም አልለያቸው አለ።

 ይሁን’ጂ ከሱዳን አውጥቶ ለኒውዚላንድ፣ ሲልም፤ ለአገረ አውስትራሊያ ነዋሪነትና ቤተሰብ ምሥረታ አብቅቷቸዋል።

My Story Abebe Tsige
አበበ ጽጌና ቤተሰቦቹ Source: Courtesy of AT

አገሩን ለሚያፈቅር ሰው ባሕር ማዶኛነት አገሩን ከውስጡ አስወጥቶ አያስረሳምና፤ አቶ አበበ ዛሬም - ከአድማስ ባሻገር ስለ አገራቸው መልካሙን ያልማሉ።

 ኢትዮጵያዊነት በምድረ ኢትዮጵያ እንዲያብብ።

የለጋ ወጣት ሕይወት ምኞታቸውም በአገረ ኢትዮጵያ ዕውን ሆኖ ለማየት ተስፋ ያደርጋሉ።

 ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ቆሞ፤ ፍትሓዊ እኩልነት ሰፍኖ።

 እስከዚያው ድረስ ግና ባሉበት አገረ አውስትራሊያ ለኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ የበኩላቸውን አስተዋጽዖዎች በመቸሩ ይገፋሉ።


Share
Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service