አንኳሮች
- የነባር ዜጎች ድምፅ ላፓርላማ ሕዝበ ውሳኔ ውጤት ከዳር እስከ ዳር 'አይሁን' ሆኗል
- ስድስቱ ክፍለ አገራትና ሰሜናዊ ግዛት 'አይሁን' ሲሉ፤ የአውስትራሊያ መዲና ግዛት 'ይሁን' ብላለች
- ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚ አውስትራሊያውያን ወደ አንድነት እንዲመለሱ አበረታተዋል
አውስትራሊያውያን የነባር ዜጎች ድምፅ ለፓርላማ በሕገ መንግስቱ ውስጥ እንዳይሰፍር ውድቅ አድርገዋል።
'አይሁን' የሚለው ድምፅ ቅዳሜ በተካሔደው ታሪካዊ ሕዝበ ውሳኔ ወቅት በሁሉም ስድስት ክፍለ አገራትና ሰሜናዊ ግዛት ተመዝግቧል።
የ'አይሁን ' ድምፅ በብሔራዊ ደረጃ የተመዘገበው አብላጫ ድምፅ በመያዝ ነው።

ከመላ አገሪቱ የአስተዳደር አካላት 'ይሁን' የሚለው ድምፅ የተመዘገበው በአውስትራሊያ መዲና ግዛት ብቻ ነው።
በቅሬታ የዋጡት ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልበኒዚ ውጤቱ "ለይቶ አይገልጠንም፤ እንዲሁም አይለያየንም"
"ከእዚህ በኋላ መሰባሰቡና ተመሳሳይ የታረቀ መዳረሻ ላይ ለመድረስ የተለየ መንገድ መፈለግ የእኛ የሁላችን ፈንታ ነው" በማለት አበክረው ተናግረዋል።

የተቃዋሚ ቡድን መሪ ፒተር ዳተን የሕዝበ ውሳኔን ሂደት "አስፈላጊ ያልሆነ" ሲሉ ጠርተው፤ አገሪቱ በኅብረት እንድትቆም ጥሪ አቅርበዋል።
"የጥያቄ አቅርቦቱና ሂደቱ አውስትራሊያውያንን በኅብረት ለማቆም እንጂ፤ ሊከፋፍለን መሆን አልነበረበትም" ብለዋል።

የተወሰኑ የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች የሕዝበ ውሳኔውን ድምፅ ውጤት ተከትለው የአንድ "ሳምንት ፀጥታ" ሲመርጡ፤ ሌሎች ከወዲሁ ቀጥሎ ምን ማድረግ እንደሚገባ ማሰብ ጀምረዋል።
የ 'ይሁን' አቋም አራማጇ የነባር ዜጎች ሚኒስትር ሊንዳ በርኒ ሕዝበ ውሳኔውን ተከትሎ የአዲሱ ትውልድ ነባር ዜጎች መሪዎች ብቅ እንደሚሉ አመኔታቸውን ገልጠዋል።
ውጤቱ የሚያመለክተው ነባር ዜጎች ምንም ዓይነት ዕክሎች ይግጠማቸው፤ አውስትራሊያውያን "የሚሹት ነገሮች እንዲከወኑ" ያመላከቱት ሁነኛ የ 'አይሁን' ዘመቻ አካሔጁ ኑንጋይ ዋረን ማንዲን፤
"ሰዎች የተወሰኑ ነባር ዜጎች ማኅበረሰባት ውስጥ የሚከሰቱ አመፅ፣ ማጎሳቆል፣ አስገዳጅ ቁጥጥርና ጎጂ ባሕሪይን አስመልክቶ ዓይን ጭፈናቸውን ማቆም አለባቸው" ብለዋል።
በ NITV የሚተላልፈውን የነባር ዜጎች አተያዮችን አስመልክቶ የ2023 ድምፅ ለፓርላማን በተመለከተ በመላው SBS አውታረ መረብ ይከታተሉ።
ከ60 በላይ ከሆኑ ቋናቋዎች ውስጥ መጣጥፎችን ለማንበብ፣ ቪዲዮዎችን ለመመልከትና ፖድካስቶችን ለማድመጥ SBS Voice Referendum portal ይጎብኙ፤ ወይም የቀጥታ ዜናዎችንና ትንታኔዎችን፣ ዘጋቢ ፊልሞችንና መዝናኛዎችን በነፃ ለመከታተል Voice Referendum hub on SBS On Demand ይጎብኙ።







