"ዕድሜ ልክ እየለመን መኖር የለብንም። የእኛ ሕዝብ አስተዋፅዖ ማድረግ አለበት፤ እንደ ሕዝብ ክብራችንም ይጨምራል" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው

Kangaroo.png

Dr Tesfaye Yigzaw, President of the Ethiopian Community Association of Victoria (L), A red kangaroo (Macropus rufus) sitting at sunset, Sturt Stony Desert, Australia (C) and Seblework Tadesse, Secretary General of the Ethiopian Community Association of Queensland (R). Credit: T.Yigzaw, Jami Tarris / Getty Images and S.Tadesse

ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበር ፕሬዚደንት እና ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ፤ የኩዊንስላንድ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ዋና ፀሐፊ፤ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላትና ማኅበራትን አስፈላጊ ሁነኛ ሚናዎች ነቅሰው ያመላክታሉ።


አንኳሮች
  • የማኅበረሰብ ማኅበራት መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር ጋር ያላቸው ግንኙነቶች
  • የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላትና ማኅበራት አውስትራሊያ አቀፍ ንቁ የፖለቲካዊ ተሳፎና ግንዛቤ ደረጃዎች
  • የሀገር አቀፍ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር አስፈላጊነትና ሚና
  • የ29ኛው ዓመታዊ የኢትዮጵያውያን እግር ኳስ ውድድር ግብዣ
  • ምክረ ሃሳብ
የኢትዮጵያውያን ማኅበር በቪክቶሪያ አለ የሚባለው ሀገር አቀፍ የኢትዮጵያውያን ማኅበር አባል አይደለንም። ከሌለ እንዲመሠረት፤ ካለም እንዲኖር እንፈልጋለን።
ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበር ፕሬዚደንት
በአውስትራሊያ ደረጃ የኢትዮጵያውያንን ጥቅም ለማስጠበቅ ሀገር አቀፍ የኢትዮጵያውያን ማኅበር አስፈላጊነቱ ትልቅ ነው። በደንብ ማጠናከሩ አስፈላጊ ነው ብዬ አስባለሁ።
ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ፤ የኩዊንስላንድ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ዋና ፀሐፊ

Share

Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now