የቫላንታይን ቀን የፍቅር መልዕክት
የኔ ደስታ አንተ ነህ። ካንተ ጋር ብቻ መሆን ይበቃኛል።
እመነኝ በየትኛውም ቦታ ሁሉ አስብሃለሁ። ስሠራ፣ ሳሽከረክር፣ ስበላ፣ ተኝቼ ዘና ስል አንተን ብቻ ነው የማስበው።
ከተመቻቹ ነገሮች ሁሉ አንተ ትበልጥብኛለህ።
ታውቃለህ? ባለፈው ዓመት ሲድኒ መጥቼ ነበር አብሬህ ያከበርኩት።
ምነው የዚያኔ አንተ ጋ በቀረሁ።
ይኸው ኮረና [ወሰን] አዘግቶ፤ በአንድ አገር ከከተማ - ከተማ መንቀሳቀስ አልቻልንም።
ቢሆንም፤ እንኳን አደረሰህ!
በጣም አፈቅርሃለሁ።
ሕይወቴ ፈገግ የምትለው ስላንተ ሳስብ ነው።
ሕይወት በቀለ ከሜልበርን ለማርቆስ በረከት ሲድኒ