አውስትራሊያ ውስጥ በየዓመቱ በጃኑዋሪ 26 የአውስትራሊያ ቀን ይከበራል፡፡ ዕለቱ በነባር ዜጎች ዘንድ በ'ኃዘን' ቀንነት ታስቦ ይውላል፡፡ በፍልሰት መጥተው አገረ አውስትራሊያን ያቆሙቱ የመጀመሪያዎቹ መርከቦቻቸው መልሕቆቻቸውን የጣሉባትን ጃኑዋሪ 26, 1788 በማሰብ በአውስትራሊያ ቀንነት ሰይመው ያከብራሉ፤ ያስከብራሉ፡፡ ኢትዮጵያውያን-አውስትራሊያውያን ዶ/ር ግርማ ሞላ፣ ዶ/ር ሰለሞን ዋስይሁን፣ ወ/ሮ ሰናይት መብርሃቱና ወ/ሮ ሃሊማ ያሲን ግለ አተያያቸውን ያንጸባርቃሉ፡፡
Share






