የውይይት መድረክ - የራያ ሕዝብ ታሪካዊ መነሻና ማንነት - ክፍል 2

Source: Courtesy of AA, BH, and TM
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የራያ ማንነት ጥያቄ አነጋጋሪ ሆኗል። በዚሁ በማንነት ጥያቄ ጉዳይ ላይ የራያ ተወላጅ ከሆኑት ወ/ሮ አስቴር አስገዶም፣ አቶ በርሄ ሐጎስና ዶ/ር ተበጀ ሞላ ጋር በውውይት መድረካችን ተነጋግረናል። ወ/ሮ አስቴር አስገዶም “ ‘ራያ የማን ነው?’ ከሚለው ራያን ማን ያስተዳድረው የሚለው ጥያቄ የሚያመች ይመስለኛል። ሁሉን አቃፊ ሲስተም መፈጠር አለበት ” ይላሉ። አቶ በርሄ ሐጎስ “የራያ ሕዝብ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ያለው። ማንነቱን ያውቃል። ስለ መላው ኢትዮጵያ ማሰብ ይሻላል።” ሲሉ፤ ዶ/ር ተበጀ ሞላ “ራያ ውሁድ ማንነት ያለው፤ ራሱን ችሎ በእግሩ የሚቆም አንድ ሕዝብ ነው ብዬ አምናለሁ” በማለት አተያያቸውን ያጋራሉ።
Share