አቶ ልዑል ፍሰሃ - በሜልተን ክፍለ ከተማ የሥራ ስልጠና ከፍተኛ ባለሙያ፣ ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ - በብሪስበን - ኩዊንስላንድ የደቡብ ማኅበረሰብ ማዕከል ማኔጂንግ ዳይሬክተር፣ አቶ ዳባሳ ዋቅጅራ - በቪክቶሪያ AMES የሠፈራ ጉዳይ ሥራ አስኪያጅና ዶ/ር ተበጀ ሞላ - በዲከን ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ፖሊሲና የማኅበራዊ ፍትሕ ጥናት ተመራማሪ፤ በኢትዮጵያ መንግሥትና በሕወሓት መካከል ሊካሔድ በዕሳቤ ስላለው የሰላም ድርድር አስፈላጊነት ግለ አተያያቸውን ያጋራሉ።
አንኳሮች
- የድርድር ስኬት ምልከታ
- የተደራዳሪዎች ሚና
- ተስፋና ስጋት
“ተደራዳሪዎች ግጭቱ ሁሉንም የሚጎዳ መሆኑን በመቀበል፣ ግጭቱን በመነጋገር መፍታት እንችላለን የሚል በጎ መንፈስን በቀዳሚነት ካስቀመጡ የድርድሩ የመሳካት ዕድል ሰፊ ይሆናል ብዬ አስባለሁ። በጥንቃቄ ከተደማመጡም መልካም ዕድሎች ይኖራሉ።” አቶ ዳባሳ ዋቅጅራ
***
“የችግሩ ምንጭ ፖለቲካው እንደመሆኑ፤ መፍትሔው ያለው ፖለቲካው ላይ ነው።” ዶ/ር ተበጀ ሞላ
***
“የፌዴራሉ መንግሥት የሚፈልገውና በተለይም የአማራ ክልል መንግሥት ፍላጎት የተለያየ ነው። ያ አንድ ሳይሆን፤ የሰላም ዝግጁነት ሳይፈጠር የሰላም ድርድር ለማድረግ ሌላ ችግር ይፈጥራል የሚል ስጋት አለኝ” አቶ ልዑል ፍሰሃ
Share






