በሜልበርን - አውስትራሊያ ነዋሪ የነበሩትን የሁለት ልጆች እናት ወ/ሮ ዓይንዋጋ አስናቀ ትኩ ሕልፈተ ሕይወትን ተከትሎ ባለቤታቸው ዶ/ር ተክቶ ካሣው፣ እህት ድርብ ካሳው ገብረመድኅን፣ የቅርብ የቤተሰብ ወዳጆች ዶ/ር ዮሐንስ አዳማ መላኩ፣ ዶ/ር ማማሩ አየነውና ዶ/ር አዳነ ዳምጠው ዓይንዋጋን በክብር ይዘክራሉ፤ ትውስታዎቻቸውን ያጋራሉ። የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ቅዳሜ ኅዳር 20 / ኖቬምበር 29 ከቀኑ 7 ሰዓት (1:00 pm) Springvale Botanical Cemetery ይፈፀማል።
አንኳሮች
- የአብሮ አደግ ሕይወት
- ከትምህርት ቤት ጓደኛነት ወደ የሕይወት አካልነት
- ዝክረ መታሰቢያ
- የምስጋናና ማፅናኛ ቃሎች
- የፀሎተ ፍትሐትና የቀብር ሥነ ሥርዓት መርሃ ግብሮች
ስለ ዓይንዋጋ ሳስብ 'የሰው ልጅ ጥሩነት ልክ ናት' ብዬ ነው የማስበው።ዶ/ር ዮሐንስ አዳማ መላኩ
Share






